ስደተኞችን ስፓንሰር ለማድረግ የወጣ የምዝገባ ጥሪ
የኢትዮጲያዊያን ማህበር በቶሮንቶና አከባቢው ከካናዳ የዜግነት እና የስደተኞች ጉዳይ መስሪያ ቤት ጋር ሰደተኞችን
ስፓንሰር ለማድረግ ባለው ስምምነት መሰረት በ 2018 ስደተኞችን ስፓንሰር የማድረግ እቅድ አለው።
1. ማህበሩ ስፓንሰር ለማድረግ ያለው ቦታ 7
2. ከስፓንሰር አድራጊው የሚጠበቅ
ከማህበሩ ጋር በሚደረገው ስምምነት መሰረት ስፓንሰር አድራጊ የሚጠበቅበት/ባት ሃላፊነት የሚከተሉት ናቸው
ለመመዝገቢያ $250 መክፈል (ይህ ክፍያ የማይመለስ ነው)
ስፖንሰር የሚደረገውን /የምትደረገውን ግለሰብ ውይም የቤተሰብ አባላት መሰረታዊ ወጪን ከመጡበት
ቀን ጀምሮ ለ 12 ወራት ለመሸፈን ፈቃደኛ በመሆን ከማህበሩ ጋር ስምምነት የሚፈርም/የምትፈርም ና
ለዚህም ዋስትና ገንዘብ በቅድሚያ የሚያሲዝ/ የምታሲዝ።
ስፖንሰር ስድራጊ መሙላት ያለበትን/ያለባትን ቅፆች መሙላት። ለዝርዝሩ
https://www.canada.ca/en/immigration-refugeescitizenship/corporate/publications-manuals/guide-private-sponsorship-refugeesprogram.html ድህረ ገፅ ይመልከቱ።
3. በስደተኞች በኩል መሞላት ያለበት ቅፅ፥
በስደተኛነት ወደ ካናዳ ስፖንሰር በመሆን ለቇሚ ነዋሪነት Permanent Residence የሚሞሉትን እና
IMM6000 በመባል በሚታወቀው መመሪያ ስር የሚጠቃለሉትን አስፈላጊ ቅጾችን በመሙላት እና
በስፓንሰር አድራጊያችው በኩል ለማህበሩ ማቅረብ።
ለዝርዝሩ https://www.canada.ca/en/immigration-refugeescitizenship/services/application/application-forms-guides.html ድህረ ገፅ ይመልከቱ።
4. የመመዝገቢያ ቦታ እና ጊዜ
ቦታ ፡ የኢትዮጵያዊያን ማህበር በቶሮንቶና አከባቢው ጽ/ቤት
1950 Danforth Avenue, East York, ON M4C 1J4
ጊዜ ፡ May 30, 2018 – June 30, 2018 ከሰኞ እስከ አርብ ከ 12pm እስከ- 5pm