ስደተኞችን ስፓንሰር ለማድረግ የወጣ የምዝገባ ጥሪ
Bishu Mamo2019-12-22T19:46:28+00:00ስደተኞችን ስፓንሰር ለማድረግ የወጣ የምዝገባ ጥሪ የኢትዮጲያዊያን ማህበር በቶሮንቶና አከባቢው ከካናዳ የዜግነት እና የስደተኞች ጉዳይ መስሪያ ቤት ጋር ሰደተኞችን ስፓንሰር ለማድረግ ባለው ስምምነት መሰረት በ 2018 ስደተኞችን ስፓንሰር የማድረግ እቅድ አለው። 1. ማህበሩ ስፓንሰር ለማድረግ ያለው ቦታ 7 2. ከስፓንሰር አድራጊው የሚጠበቅ ከማህበሩ ጋር በሚደረገው ስምምነት መሰረት ስፓንሰር አድራጊ የሚጠበቅበት/ባት ሃላፊነት የሚከተሉት ናቸው ለመመዝገቢያ $250 መክፈል (ይህ ክፍያ የማይመለስ ነው) ስፖንሰር የሚደረገውን /የምትደረገውን ግለሰብ ውይም የቤተሰብ አባላት መሰረታዊ ወጪን ከመጡበት ቀን ጀምሮ ለ 12 ወራት ለመሸፈን ፈቃደኛ በመሆን ከማህበሩ ጋር ስምምነት የሚፈርም/የምትፈርም ና ለዚህም ዋስትና ገንዘብ በቅድሚያ የሚያሲዝ/ የምታሲዝ። ስፖንሰር ስድራጊ መሙላት ያለበትን/ያለባትን ቅፆች መሙላት። ለዝርዝሩ https://www.canada.ca/en/immigration-refugeescitizenship/corporate/publications-manuals/guide-private-sponsorship-refugeesprogram.html [...]